“ሕያው
ታሪክ በሕያዋን ምስክርነት”
የተሰኘው ይህ መጽሐፍ 300 ገጾች ያሉት በ31 ምዕራፎች የተከፈለና ከ140
በላይ ንኡሳን አርእስት ያሉት ነው ። መጠኑን ለመቀነስ ሲባል ሁሉም አርእስት በማውጫው
ስላልተጠቃለሉ
መጽሐፉን በመገላለጥ ይምረጡ ።
የመጽሐፉ
አብዛኛው ክፍል በቀጥታ የብፁዕ ወቅዱስ ዶ/ር አቡነ ጳውሎስ ቀዳማዊን የሕይወት ታሪክ
ከልደት
እስከ ሕልፈት ድረስ ይዟል ።
ቀሪውና
አናሳው ክፍል ደግሞ ከዚሁ ከ5ኛው ፓትርያርክ ጋር ተያያዥ የሆኑ ታሪኮችን ለማጠቃለል በማሰብ ከኢትዮጵያ
መንበረ ጵጵስና አመሠራረት በመነሣት የ4ቱን ፓትርያርኮች ታሪክ ባጭሩ በመተረክ የ4ኛውን ፓትርያርክ ከሥልጣን መውረድ በተመለከተም በቋሚ ምስክሮች የተደገፈ እውነትን ለኢትዮጵያውያን
ይፋ ያደርጋል ።
ይህ
መጽሐፍ ባጭሩ ሲገለጽ ለ20 ዓመታት ቤተ ክርስቲያንን የመሩት 5ኛው ፓትርያርክ ማን እንደ ነበሩና በተጨባጭ
ማስረጃና በቋሚ የዐይን ምስክሮች በመደገፍ በሥራቸው አስደናቂና ልዩ መሪ እንደ ነበሩ ይናገራል።
5ኛው
ፓትርያርክ ከዚህ ዓለም በሞተ ሥጋ በተለዩ ጊዜ የ20 ዓመታት ሥራቸውን በጥንቃቄ ሲመለከቱ የነበሩ :: በአገር ውስጥና
በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ታዋቂ የሃይማኖትና የሕዝብ መሪዎች የሰጡትን እጅግ አስደናቂና ያልተለመደ ምስክርነትንም በከፊል ይዟል ።
ለመግዛት ይህንን ይጫኑ/To buy the booksgo to Amazon
https://amzn.to/2Q2Bw94
ከመጽሐፍ ቅዱስ
ጋር ይተዋወቁ
የተሰኘው
ይህ መጽሐፍ ሦስት ምዕራፎችንና አሥር አበይት ክፍሎችን የያዘ ሲሆን በመጽሐፍ ቅዱስ ዙሪያ በአማርኛ
ቋንቋ ከተጻፉ መጻሕፍት ሁሉ ባቀራረቡና በይዘቱ ፍፁም የመጀመሪያው ነው ።
ስለመጽሐፍ
ቅዱስና በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስላለው ሁሉ በዚህ መጽሐፍ ተካቶ ይገኛል ። በቂ ግንዛቤ ከሌላቸው ጀማሪዎች
እስከ መጽሐፍ ቅዱስ መምህራን ድረስ ከዚህ መጽሐፍ የማይለካ ዘርፈ- ብዙ እውቀትን ያገኛሉ
https://amzn.to/2Q2Bw94
፤ ይማሩበታል
ያስተምሩበታልም ።
ስለዚህ ስለእምነትዎ
በሚገባ በማወቅም ሆነ በማሳወቅ ራሰዎን ፤ ቤተሰበዎንና ሕብረተሰቡን ሕያው
በሆነው በሕያው
እግዚአብሔር ቃል ማነጽ ከፈለጉ ፤ ስለ እያንዳንዱ እምነት መጽሐፍ ቅዱስ ምን እንደሚል ፤የተለያዩ የሃይማኖት
ተቋማት የሚቀበሉት መጽሐፍ ቅዱስ እርሰዎ ከያዙት ጋር የሚመሳሰል ወይም የሚለያይ መሆኑን
ማወቅ የሚሹ ከሆነ ፤ ስለመጽሐፍ ቅዱስ የማስተማርና የመስበክ ሃላፊነት ካለብዎ ፤ የሰንበት ትምህርት ቤት
ዘማሪ ፤ ዲያቆን ፤ ቄስ ፤ መነኩሴ ፤ ጳጳስ ፤ ኤጲስ ቆጶስ ወዘተ ከሆኑ፤ ወይም በመጽሐፍ ቅዱስ ዙሪያ ጥናት የሚያካሂዱ
ከሆነ ፤ በአጠቃላይ ፍፁም የሆነውን
ሃይማኖታዊውንና ማኅበራዊውን ሕገ-መንግሥት ሊመሩበት ከወደዱ ፤
ከዘፍጥረት እስከ ራእየ-ዮሐንስ እንዲሁም 2ኛ የቀኖና መጻሕፍትን ጨምሮ በ81ዱ ፤ በ76ቱ ፤ በ73ቱ ፤በ66ቱና
በ24ቱ የዕብራውያን ብሉይ ኪዳን የሚገኙ መጻሕፍት ሁሉ በቀላልና ልዩ በሆነ ዘመናዊ አቀራረብ የመጽሐፉ
ጸሐፊ ፤ የተጻፈበት ዘመንና ቦታ ፤ የመጽሐፉ ፍሬ-ሐሣብ ባጭሩ ፤ የመጽሐፉ ጠቅላላ ይዘት ባጭር ትንታኔ፤
ምርጥ
ጥቅሶች ፤ ልዩና ያልተለመዱ ፤ እንዲሁም የመጽሐፉ መልዕክት በሚሉ መሠረታውያን አርእስት የያንዳንዱ መጽሐፍ
ይዘት ማራኪ በሆነ መንገድ የመጽሐፉን ጠቅላላ ሐሣብ ባጭሩ ተምሮ በሰፊው መረዳት በሚያስችል ዘዴ ቀርቧል
።
በእኔ
እይታ የክርስትና እምነት ተከታይ የሆነ ሁሉ ከልጅ እስካዋቂ ይህንን መጽሐፍ ሊይዝ ይገባል
እላለሁ ። በመሆኑም እርሰዎም ከመጽሐፍ ቅዱሰዎ ጋር ተዋውቀው ያስተዋውቁት እላለሁ ።
የዘመኑ ታሪክ
ስለዘመናት
አቆጣጠር ቤዓለም ዙሪያ፤ ስለክርስቶስ የልደት ቀን፤ ስለ ዓመተ ምሕረት መጀመሪያ ወር ወዘተርፈ ከአሁን በሁዋላ ጥያቄ አይኖርም። ሁሉንም ከዚህ መጽሐፍ በማያሻማ ሁኔታ እስከ ማስረጃው ያገኙታል፡ የዚህ መጽሐፍ ዋና አላማ በታሪካዊ እውነት ላይ በመመርኮዝ ለብዙኃኑ ጥያቄ በተቻለ መጠን ምክንያት ወይም ማስረጃ ያለው መልስ መስጠት ነው፡፡ በዓለማችን የሚገኙ ቢያንስ ክ40 በላይ የሚሆኑ የዘመን ቆጠራ ስልቶች በጣም የተለያየና የተራራቀ ወይም የማይገናኘ የዘመን ቁጥርን ያሳዩናል ምክንያቱን ከዚሁ መጽሐፍ ያገኙታል። እንዲሁም የ10 ዓመታት የበ ዓላትና የአጽዋማት ማውጫ ካላንደር አብሮ ተካቶ ይገኛል። ከሁሉም በላይ ጊዜ ወርቅ ነው በማለት እግዚአብሔር የለገሰለዎን ጊዜ ወርቅነቱን አውቀው እንዴት ሊጠቀሙበት እንደሚችሉ አበክሮ ይመክረዎታል። መጽሐፉ ለስጦታ አመች ሆኖ ስለተዘጋጀ ይህንን ወርቅ የሆነ ስጦታ ለሚወዱዋቸው ገዝተው መስጠት ይችላሉ::
|
የቋንቋ ውበት፡
ይህ
የቋንቋ ውበት የተባለው መጽሐፍ የዕውቅ ግጥሞች ስብስብ ነው፡፡በዚህ የዕውቅ ግጥሞች ስብስብ መጽሐፌ ውስጥ ያካተትኳቸው ሥነ ጽሁፎች ከ1979 እስከ 2000 (የኢትዮጵያ ሚሊኒየም) ዓ/ም ድረስ ከጻፍኳቸውና በምሁራን ዘንድ ተወዳጅነትን ከተቀዳጁት ከብዙዎቹ ግጥሞቼ መካከል በውበታቸውና በስሜት ኮልኳይ ባሕርያቸው ጉድና ድንቅ የተባለላቸውን፤ልባዊ የሆነ የአድናቆት ሳቅ የተሳቀላቸውን የደስታ ዕንባ የተነባላቸውን፤ዓለም ከመቀመጫው ብድግ ብሎ አዳራሾች እስከ ሚነዋወጡ ያጨበጨበላ ቸውን፤የክብር መዛግብት ብሎ በሰየማቸው ዓለም አቀፍ የግጥምና ቅኔ መዛግብቱ (መጻሕፍቱ) የመዘገባቸውንና ውድና ድንቅ ሽልማቶችን ለውበታቸውና ለጥዑም አንደበታቸው ያበረከተላቸውን በቁጥር ውሱን፤በደረጃ ግን አንደኛ የሆኑትን ብቻ በማሰባሰብ ነው፡፡
በዚች መጽሐፍ የሚገኙት ግጥሞች አብዛኛዎቹ አዳዲሶች ሲሆኑ ‹‹የጸጋ ግምጃ ቤት›› ከተሰኘው መጽሐፌ የተወሰዱም ብዙ ግጥሞች ይገኛሉ፡፡ ይህ የግጥም መጽሐፍ ሃይማኖታዊ፤ማኅበራዊና ፖለቲካዊ በሚሉ ሦስት አበይት ሐሣቦች ዙሪያ በማተኮር ጠቅላላ የሕይወት ክስተቶችን ያጠቃለለ ሲሆን የቅኔን አነጋገርና የቋንቋን ሁለንተናዊ ውበት ቁልጭ ጥርት አድርጎ ያሳያል፡፡ መጽሐፉ የቋንቋን ኅብርና ሰምና ወርቃዊ ውበት ማስተማርያ እንዲሆን ስለታሰበ በጥያቄና በመልስ መልክ ጭምር የቀረበ ናነው፡፡ከዚህ መጽሐፍ ሰምና ወርቅን፤ኅብርንና ታሪክን መሠረት ያደረጉ ከሰው ልጅ ውስጣዊ ስሜት ጋር በቅጽበት ለመዋሐድ ጊዜን የማይወስድባቸው ሕይወት አቀፍ ድርሰቶችን ያገኛሉ፡፡
|
ግራኛዊው አዋጅ
በኢትዮጵያ
ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ከግራኝ መሐመድና ከጉዲት ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ቤተክርስቲያናችንን ያዋረደና ሰብአዊና ሃይማኖታዊ ክብራችንን ያለገደብ የነካውን ካህንና ዶክተር ነኝ ባይ ከሁሉም በላይ በቀጥታ እግዚአብሔር ጠራኝ የሚለውን ተመጻዳቂውን ሰው የደ/ር ፓስተር ቶሎሳ ጉዲናን የክህደትና የድፍረት ትምህርት (አዋጅ ብለው ይቀላል) በመቃወም ተጨባጭና አጥጋቢ መልስ የሚሰጥ፤ የቤተ ክርስቲያንን
አኩሪ ታሪክና፤ለመላው ኢትዮጵያዊና ኢትዮጵያ ያበረከተቺውን እንዲሁም ያለማቋረጥ የምታበረክተውን የማይለካ ማሕበራዊ፤ ሐይማኖታዊና መንግሥታዊ ጥበብ ቁልጭ አድርጎ የሚያስረዳ ኦርቶዶክሳውያን ብቻ ሳይሆኑ ማነኛውም ኢትዮጵያዊ ሁሉ ይልቁንም እርስ በርስ ተከባብረው የሌላውን ሰብአዊ ክብርና ሃይማኖታዊ ነጻነት ሳይጋፉ፤የራሳቸውን ክብርና ነጻነት ሳይቀሙ መኖርን የሚሹና የሚወዱ ሰላማውያን ሁሉ፤ከሁሉም በላይ‹‹በአንተ እንዲደረግብህ የማትፈልገውን በሌላው ላይ አታድርግ፤ ለአንተ እንዲደረግልህ የምትሻውን ለሌላው ደግሞ አድርግ››የሚለውን ቅዱስ መርሕ ያልዘነጉ ሊያነቡትና እንደታሪክ ሊያስቀምጡት የሚገባ ታሪካዊ መጽሐፍ ነው፡፡ይሀ መጽሐፍ በመላዋ ኢትዮጵያና በሰሜን አሜሪካ የሕዝብም ሆነ የሐይማኖት ቤተመጻሕፍት እንዲሁም መዝሙር ቤቶችና የቤተክህነት ማዕከላት ይገኛል፡፡
ሀብታችንና ሥርዓቱ
‹‹ነገር ግን
ሁሉም በአግባብና በሥርዓት ይሁን›› 1ኛ ቆሮ.14፣40 በዚህ መጽሐፍ በምሳሌነት ከህገ-ልቡና ጀምሮ እስከ ሕገ-ሐዲስ ወይም እስከ አማናዊቷ ቤተክርስቲያን ድረስ ያለው የታሪክ ትስስር፤ የእውነተኛዋ ቤተክርስቲያን አካላዊና መንፈሳዊ አመሠራረት፤ አሠራር፤ አከፋፈልና ስያሜ፤ ክልሏን ከሚጠብቁ አጸውተ-ኆኅት ወይም የጥበቃ ክፍሎች ጀምሮ መሠረቷና ጉልላቷ ወይም የክርስቶስ ምድራዊ ወኪል እስከ ሆነው እስከ ፓትርያርክ ድረስ ያለው የመንፈሳዊ ሥልጣን አመዛዘንና አሰያየም፣ (አሿሿም፤) መዋቅርና ሕልውና በአጠቃላይ የጾታ ምዕመናን ልዩ ልዩ አከፋፈልና የሥራ ድርሻ ሌሎችም የእምነታችን ቁልፍ ትምህርቶች ተካተው ይገኙበታል፡፡ መጽሐፉ ዓለም አቀፋዊ ይዘት ያለው የጥናት ጽሁፍ ስለሆነ በከፍተኛ ትምህርት ለሚገኙ ወይም በጥናት ሥራ ለተሰማሩ ሁሉ እጅግ ጠቃሚ ነው፡፡በመላዋ ኢትዮጵያ የመጻህፍት ሱቆችና በሰሜን አሜሪካ በተለይ በዲሲና አካባቢዋ በሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናትና እንዲሁም በኢትዮጵያውያን የገበያ ማዕከላት ያገኙታል፡፡ (በቅርብ ጊዜ በሲዲ ይዘጋጃል)
የጸጋ ግምጃ ቤት
የጸጋ
ግምጃ ቤት የተሰኘው ይህ መጽሐፍ በብዙዎቹ የታወቁና በሊቃውንቱም ዘንድ ታላቅ አድናቆትን ያተረፉ ማሕበራዊውን፤ ሐይማኖታዊውን፤ እንዲሁም ፖለቲካዊውን የሕይወት መስመር ሁሉ የሚቃኙ ልዩ ልዩ የአማርኛ ሰምና ወርቅ የግጥም ድርሰቶችን በዘመናዊ ስልት ሰብስቦ የያዘ ሲሆን በውስጡ ከተካተቱት ሥነ-ጽሁፎች መካከል በሰው ልጅ ምድራዊና ሰማያዊ ሕይወት ውስጥ የሚታዩና ሊታዩ የሚችሉ ልዩ ልዩ ክስተቶችና መፍትሔዎቻቸው ጭምር፤ ከ1979 ዓ/ም ጀምሮ እስከ 1989 ዓ/ም ድረስ በወቅቱ በአበይት ታሪክነታቸው የታወቁ አሰቃቂም ሆኑ አስደሳች አንኳር ድርጊቶች ስሜት ኮልኳይ በሆኑ የግጥም ስንኞች በድርሰት መልክ ተካተው ይገኙበታል፡፡
የምስጋና፤የጸሎት፤
የደስታና የኀዘን ቅኔዎችንም ቀላልና ግልጽ በሆኑ ቃላት አቀነባብሮ ይዟል፡፡ በተጠቀሱት የአማርኛ ሰምና ወርቅ የግጥም ድርሰቶች • ራስዎን ያዝናናሉ፤ • ከኀዘንዎ ይጽናናሉ • ደስታዎንም ከልኩ እንዳያልፍ ይቆጣጠራሉ፡፡ መጽሐፉ የሚገኘው አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኙ የቤተክህነት የመጻሕፍት ሱቆች ብቻ ነው፡፡
|
የፍቅር ምሥጢር 1ኛ
‹‹መጋባት በሁሉ
ዘንድ ክቡር መኝታውም ንጹሕ ይሁን›› ዕብ.13፣4 ይህም መጽሐፍ የፍቅር ምሥጢርና ትንሿ ወይም አዲሷ ቤተክርስቲያን የተባለቺውን ማንነት፣በጋብቻ የሚዋሐዱ የሁለት ተቃራኒ ጾታዎች ፍቅር ከሥነ-ተፈጥሮ ጋር የተመሠረተ፤ልዩና ጥልቅ ምሥጢር እንዳለው፤ምሥጢሩም እንዴት እንደሆነ ምንና እንዴት እንደሆነ እስከ ማስረጃው፤በሁለት የጋብቻ ምርጦች መካከል የሚጣለው የግብረ-ሥጋ ግንኙነት ማዕቀብ በትዳር ላይ የሚፈጥረው ችግርና ችግሩ ምን እንደሆነ፤ ኤድስ መከላከያም ሆነ መድኃኒት በትክክል እንዳለው፤ አራቱ የጋብቻ ዓይነቶች የትኞቹ እንደሆኑ፤የሚሉና ሌሎችም በትዳራችን መካከል አዘውትረው የሚከሰቱ ችግሮችን ከመፍትሔዎቻቸው ጋር አካቶ የያዘ ሲሆን ፍቅርና ሰላም የሰፈነበት የተሳካ ጋብቻን መገንባት የሚያስችል መንፈሳዊ ጥበብን ይጋብዘናል፡፡
በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ያሉትን የጋብቻ መፍትሔዎችና ትክክለኛ ሐሳቦች በሌላ በማንም ሃይማኖታዊ የጋብቻ መጻህፍት ውስጥ በፍፁም አያገኟቸውም፡በአጠቃላይ መልኩ ሁለት ተቃራኒ ጾታዎች ከጋብቻ በፊት፤ በጋብቻ ጊዜ፤ ከጋብቻም በኋላ ሊፈጽሟቸው የሚገባቸውን የያንዳንዳቸውን ፆታዊና ጋብቻዊ ድርሻዎችን አንድ በአንድ በመተንተን የጋብቻን ትርጉምና ጠቅላላ ይዘት ያስተምራል፡፡ይህም በመጽሐፍና በካሴት መልክ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡ በቪዲዮ በድራማ መልክም ለማዘጋጀት ታቅዷል፡፡
|
ለመግዛት ይህንን ይጫኑ/To buy the booksgo to Amazon
|
No comments:
Post a Comment