Blog Archive

Patriarches

ውነ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ኤጲስ ቆጶስ

















ከአቡነ ሰላማ ሞት በኋላ የጵጵስና ሥልጣን ከኢትዮጵያውያን ወጥቷል፡፡
የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ከግብፅ ቤተክርስቲያን ከመንበረ ማርቆስ ጳጳሳት 
እየተላኩላት ለ1600 (ለአንድ ሺህ ስድስት መቶ) ዓመታት አካባቢ የቆየች ሲሆን 
በነዚህ ዓመታት ውስጥ አንድ መቶ አሥራ አንድ (111) (111ኛው አቡነ ባስልዮስ 
ናቸው ይባላል) ጳጳሳት ተልከውላታል፡፡ 

በዚህ ሁኔታ ከቆየች በኋላ በክርስቲያን ነገሥታትና በሊቃውንቷ የረጅም ጊዜ ጥረት 
ከሊቃውንቷ መካከል መንፈሳዊ መሪዎቿን እንድትመርጥ ተፈቅዶላት ራሷን ለመቻል በቅታለች፡፡ 

ኢትዮጵያ ከራሷ ሊቃውንት ጳጳሳትን መሾም የጀመረቺው ግንቦት 25 ቀን 1921 ዓ/ም ሲሆን 
ሊቀጵጵስናን በ1943 ዓ/ም ሾማለች፡፡

 ፓትርያርክ (ፓትርያርክነትን) ደግሞ በ1951 ዓ/ም ነው፡፡ የመጀመሪያው ሊቀጳጳስና ፓትርያርክ 
አቡነ ባስሊዮስ ናቸው፡፡ እስከ አሁን ድረስ 109 ኤጲስቆጶሳትንና ሊቃነ ኤጲስ ቆጶሳትን 
እንዲሁም አምስት (5) ፓትርያርኮችን የሾመች ሲሆን 5ኛውና 4ኛው በሕይወተ ሥጋ ይገኛሉ፡፡ 

በመንበሩ ያሉት 5ኛው ፓትርያርክ ‹‹ብፅዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት 
ወፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ ሊቀጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት››
ተብለው ይጠራሉ፡፡

4ኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ በሕይወተ ሥጋ ያሉ ሲሆን 
በሰሜን አሜሪካ ይኖራሉ፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በአሁኑ ጊዜ 
45 ሚሊየን ምዕመናን፤40 ሺህ አብያተ ክርስቲያናትና ገዳማት፤5 መቶ ሺህ
(500.000) ካህናት ያሏት ሲሆን 8 ከሀገር ውጪ 40 በሀገር ውስጥ የሚገኙ 
በጠቅላላው 48 አህጉረ ስብከት አሏት፡፡

 በተጠቀሱት አህጉረ ስብከትና በመንበረ ፓትርያርክ በልዩ ልዩ አገልግሎት የተመደቡ 
የቤተክርስቲያኗ ጠባቂዎችና የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት የሆኑ 60 ሊቃነ ኤጲስቆጶሳት
 አንድ ፓትርያርክ ይገኛሉ፡፡

No comments:

Post a Comment