Blog Archive

poetry

ልዩ ልዩ ግጥሞች


የሚፈልጉትን የግጥም ዓይነት ለማንበብ ከማውጫዎች መካከል ይምረጡና ይጫኑ ወይም ይንኩ
ግጥም፡ ሁሉ ቅኔ ላይኖረው ቢችልም ቃላትን ስሜት ኮልኳይ በሆነ መልኩ አቀነባብረው
 ካቀረቧቸው ከቅኔ ባላነሰ ደረጃ ማራኪና ስሜት ኮልኳይ የሆነ የሥነ ጽሁፍ ዓይነት መፍጠር ይቻላል፡፡
በዚህ ድረ-ገጽ ሃይማኖታዊ፤ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ በሚሉ ሦስት አበይት ሀሣቦች ዙሪያ ያተኮሩና
ጠቅላላ የሕይወት ክስተቶችን ያካተቱ፤ ከሰው ልጅ ውስጣዊ ስሜት ጋር በቅጽበት ለመዋሐድ ጊዜን
የማይወስድባቸው ልዩ ልዩ ሰምና ወርቅ እንዲሁም ኅብር ግጥሞችን ያገኛሉ። ከነዚህ ግጥሞች
የቅኔን አነጋገርና የቋንቋን ሁለንተናዊ ውበት ይማራሉ።



THE LAND OF COLLECTION
You are wise and beautiful
So pretty and attractive
Every body in your love
  Has been fallen
The land of collection
Has loved you all the nation
Black, white, and Hispanic
Japheth, ham, and Semitic
From four sides of the earth
East, west, north, and south
Every season without limit
Every time day and night
Unexceptional, all human being
Is flowing to you more and more
Refusing his homeland to come here.
Point at you the world’s eyes
All believe you as land of the promises
A special land full of hopes
As Jerusalem the land of our Jesus
Your name, your flag, and your dollars
Have been worshiped from others
All mankind female and males.


ወጣት ሽማግሌ አይመጥን ዕድሜን
ወንድና ሴት ብሎ አይከፍል ፆታን
ሃይማኖት አይገታው ሞስሊም ክርስቲያን
ሕግ አይከለክለው አያዘው ቁርዓን
እምነት ልጓም የለው ፈረስ ቢን ላደን፡፡

 In the presence of His Holiness D/r Abune Paulos The Patriarch of Ethiopian Orthodox Tewahedo Church

ሁሉንም በወቅቱ ጠብቆ ጊዜውን
በጥበብ በሥልጣን የሚያደርግ ሥራውን
ፈጥሮ የሚገዛ የሚያዝዝ ሁሉንም
እርሱ ካልፈቀደ ቸሩ መድኃኔ ዓለም
እንኳንስ በሰው ልጅ በደቂቀ አዳም
 ከዛፍ ከቅርንጫፍ ከግንዱ ቢሆንም
ቅጠል በነፋስ ኃይል ሊነጥብ አይችልም፡፡

ስለዚህ በቃሉ የሆነው በአንተም
ምርጫህ አጋጣሚ ግብታዊ አይደለም፡፡

አቅዶ ወስኖ ልዑል እግዚአብሔር
 በፍና አሜሪካ በደማስቆ ምድር
በቃል ጠራህ እንጂ ለዚህ ታላቅ ምሥጢር፡፡

ጳውሎስ በውስጥሺ የተጠራብሺ
አንቺስ አሜሪካ ደማስቆ ነሺ፡፡

በደማስቆ ደብር በአሜሪካን
ጳውሎስ ሲመረጥ በአምላካችን
በድንገት ከሰማይ ተከስተ ብርሃን፡፡
መጣልሽ ዳግመኛ
አንቺ ኢትዮጵያ የአገር ደገኛ
ጽኑ እምነት ያለሽ እጅግ ጸሎተኛ
የተመረጥሺ ነሽ በጣም እድለኛ፡፡
የዓለም ብርሃን የወንጌል አርበኛ
ሐዋርያው ጳውሎስ መጣልሽ ዳግመኛ፡፡

አንተስ ሙሺራችን ጻድቅ ነህ በውነት
የገነት ጠባቂ መላከ ሕይወት
እየመራ አስገባህ በቁምህ ገነት፡፡
በሰማይ ናት ብዬ በምኞት ሳያት
ለካስ በምድር ላይ ኖራለች ገነት፡፡
ዕድልህ የለማ ጋብቻህ አዲስ
ለጽድቅ ስለጠራህ ሕያው ክርስቶስ
በገነት ከተማ በል ተመላለስ፡፡
ካልሞላ በስተቀር

(የዲ/ ሞላና የመብራት ጋብቻ)
ሳይጸልይ አያድርም ከዳዊት ጸሎት
ቀን በፀሐይ ብርሃን ሌሊት በመብራት
ለሰኔ ሚካኤል ሻማ ተስለህ
ስዕለትህ ሰምሮልህ መብራትህን ያዝህ
ማድረስ እንድትችል የሌሊት ጸሎት
ምንጊዜም ትኑርህ የራስጌ መብራት፡፡
መጠጥ ስታስቀዳ ውሃ እንኳን ሳይቀር
የጎደለ አትጠጣም ካልሞላ በስተቀር፡፡

ጳጳሱም ይሳቅ
(ብፁዕ አቡነ ይስሐቅ በተገኙበት የቀረበ)

እውነቱን ገልጨ ምንም ሳልደብቅ
ምሥጢር አወራለሁ በሰምና ወርቅ
ሁሉም ደስ ብሎት ከልጅ እስከ ሊቅ
ለበአል የመጣው ምዕመኑ፤ ዲያቆኑ፤
ካህኑ፤ ጳጳሱም ይሳቅ፡፡

No comments:

Post a Comment