Blog Archive

Saturday, July 19, 2014

Ethiopia The Home-Land of God

ኢትዮጵያ ሐገረ -እግዚአብሔር (የእግዚአብሔር አገር)



ነፍስ ካወቅንባት ቅጽበት ጀምሮ በጆሯችን እንደ ጠገብነው ኢትዮጵያ የእግዚአብሔር አገር፤ የሃይማኖት መዲና፤ ወይም ማዕከል ትባላለች፤እውነትም ናት፡፡ ከሥጋዊ ድሃነቷ ወይም ችግረኛነቷ ጋር እንኳን እምነቷ አይዛባም፡፡ እግዚአብሔር ጸጋውን አድሏታል፡፡ 

የእግዚአብሔር እስትንፋስ የሆነው የመጻህፍት ሁሉ አባት መጽሐፍ ቅዱስ እንኳኢትዮጵያወይም ኩሽ የሚለውን ቃል ወይም ስም 17 የመጽሐፍ ቅደስ ክፍልች 47 ጊዜ  ጠቅሶት ይገኛል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ከሚያተኩርባቸው አበይት ነጥቦች መካከልም መልክኣ ምድሯ፤ እምነቷ፤ ደግነትዋና ከእግዚአብሔር ጋር ያላት ጽኑ ፍቅር ጥቂቶቹ ናቸው፡፡

ስለኢትዮጵያ ታላቅነት፤ ስለሕዝቧ ዕፁብ ድንቅ ተፈጥሮ፤ባህልና ጠባይ እንዲሁም ትሕትናና እምነትን የተላበሰ አስተዋይነት መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ሳይሆን የዓለማችን ታላላቅ ጠበብትም ብዙ ተናግረዋል፡፡

ከብዙዎቹም ጥቂቶቹን ለመጥቀስ ያህል ከክርስቶስ በፊት በ8ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የነበረው ታላቁ የግሪክ ባለቅኔ ሆሜር ‹‹ ኢትዮጵያውያን በጉልበት ኃያላን፤ በመልክ የተደነቁ፤ በውበት የተዋቡ፤በጠባያቸውም ትሕትናን የተላበሱ አስተዋዮች ናቸው›› ሲል የምዕራቡ ዓለም የታሪክ አባት እየተባለ የሚጠራው ሔሮዶቶስ በበኩሉ ‹‹ ኢትዮጵያውያን በውበት፤ በቁመትና በኃይል የተለዩ፤ የተደነቁም ናቸው›› ብሏል፡፡

እንዲሁም ታላቁ የዓለም የሥነ-ጽሁፍ አባት የሆነው እንግሊዛዊው ዊሊያም ሸክስፒር ኢትዮጵያውያን ማራኪና በመንፈሳዊም ሆነ በሥጋዊ ውበት የታደሉ ውቦች መሆናቸውን ማራኪና ውብ በሆኑት በታወቁት የፍቅር ግጥሞቹ ወይም ቅኔዎቹ አሳምሮ ገልጦታል፡፡ ሲሉ የታሪክ ጸሐፊዎች መዝግበውት ይገኛሉ።

ታዲያ ይህ ሁሉ ዓለምን የሳበው ውበት በደረቁ ሥጋዊ ውበት ብቻ ሳይሆን መንፈሳዊ ጸጋም ጭምር ስለተዋሐደው ነው፡፡ 

በመሆኑም እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያንን በተለየ ፍቅር እንደ ሚወዳቸው ወይም እንደ ሚወደን በቃል ብቻ ተወስኖ ወይም በመጻሕፍት ብቻ ተመዝግቦ አልቀረም፡፡ ነገር ግን ተጨባጭ የሆነና ከዓለም የተለየ ክብርና መንፈሳዊም ሆነ ሥጋዊ ዝናን ከነሙሉ ታሪኩ አጎናጽፎናል፡፡ ይህ እውነተኛ ፍቅር ከተገለጠባቸው መካከልም የሚከተሉት ዓለም አቀፍ የታሪክና የእምነት ቅርሶች ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ እነዚህም
 
1ኛ. ከዓለም የተሰወረውና በየትም ዓለም የማይገኘው፤በራሱ በእግዚአብሔር ጣቶች አሠርቱ ቃላት ወይም ትእዛዛት የተጻፉበት የቃል ኪዳን ጽላት (ታቦት) በርእሰ-አድባራት አክሱም ጽዮን የሚገኝ ሲሆን በ957ዓ/ዓ በንግሥት ሳባ ጊዜ በኢትዮ እሥራኤላዊው ወጣት ንጉሥ በቀዳማዊ ምኒልክ አማካኝነት ወደ ኢትዮጵያ የገባ ነው፡፡

2ኛ. ለዓለም ድኅነት ሲል በቀራንዮ አደባባይ መለኮታዊ ሕይወቱን የሠዋበት ግማደ መስቀል (የመስቀሉ ቀኝ ክንፍ ወይም ክፍል) በደብረ-ከርቤ ግሸን ማርያም ቤተክርስቲያን ውስጥ የሚገኝ ሲሆን ወደ ኢትዮጵያ የገባው በ14ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በዐፄ ዳዊት ጊዜ በአቡነ ዮሐንስ የኢየሩሳሌሙ ፓትርያርክ አማካኝነት ነው፡፡

3ኛ. ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስ ለመጀመሪያ ጊዜ የሳላት የመጀመሪያዋ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ስዕል (ምስለ ፍቁር ወልዳ) ወይም ስዕለ አድኅኖ (ፈዋሽ ስዕል) በደብረ ዘመዳ ገዳም የምትገኝ ሲሆን ወደ ዚህ ገዳም (ወደ ኢትዮጵያ) የገባቺው በ14ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በዐፄ ዳዊት ጊዜ በአቡነ ዮሐንስ የኢየሩሳሌሙ ፓትርያርክ አማካኝነት ከግማደ መስቀሉ ጋር እንደ ነበረ ታሪክ ይናገራል፡፡

4ኛ. የሰብአዊውን ፍጡር ቅድመ ታሪክ ያበሠረውና በዓለም አቀፍ ጠበብት የታሪክ ደረጃ የተሰጠው የሉሲ ወይም በኢትዮጵያዊ ስሟ የድንቅነሽ አጽም በ1974 ዓ/ም ከከርሰ ምድር ውስጥ የተገኘው እውነት ነው፡፡

እነዚህ ከዚህ በላይ የተጠቀሱት ጥቂቶቹ ሲሆኑ ሌላው ታላቁ ስጦታዋ ደግሞ በማንም አገዛዝ ሥር ያልወደቀች፤

በምታምነውና በሚወዳት በልዑል እግዚአብሔር ኃይል ተጠብቃ የምትኖር፤የራሷ ፊደል፤ቋንቋ፤አኃዝ፤ዕፁብ ድንቅ የሆነ ባህልና የሥነ-ጽሁፍ ስልት ያላት ብቼኛዋ አፍሪካዊት አገር መሆኗ ነው፡፡

To watch video please click this

No comments:

Post a Comment