ሲያቀብሉና ሲቀበሉ
ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን የሚያቀብሉ ካህናት ለሚቀበሉ ሁሉ ስለሚያቀብሉት
ቅዱስ ሥጋና ክቡር ደም እንደ ሚከተለው የአምላካችንን ቸርነትና የድኅነት
ሥራ በሚመሰክሩ ኃይለ ቃላት በአዋጅ እንዲያስረዱ ወይም ምሥክርነታቸውን እንዲሰጡ ግድ አለባቸው። እርሰዎም ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ሲቀበሉ
አዋጁን ሰምተው መልእክቱን ወይም አዋጁን ተረድተው በሥርዓቱ መሠረት አሜን ወይም ይሁን ይደረግ በማለት ይቀበሉ።
በመቅደስ ውስጥ በካህናት
መካከል የሚደረግ የቅዱስ ቁርባን ሥርዓት
ካህኑ ቅዱስ ሥጋውን በመቅደስ ውስጥ ለካህናት ሲያቀብል
በጌታ ቅዳሴ ወይም በቅዳሴ እግዚእ፦ “ ሥጋሁ ለእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ለቀድሶ ሥጋ ወነፍስ ወመንፈስ” ወይም በአማርኛ
“ሥጋንና ነፍስን ደመ ነፍስንም ለማክበር የሚሆን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋ ይህ ነው”
በሐዋርያት ቅዳሴ ወይም በቅዳሴ ሐዋርያት፦ “ ኅብስተ ሕይወት ዘወረደ እምሰማያት ቅዱስ ሥጋሁ ለክርስቶስ”
ወይም በአማርኛ “ከሰማይ የወረደ የሕይወት ኅብስት የሚሆን የክርስቶስ ክቡር ወይም ቅዱስ
ሥጋ ይህ ነው”
በሊቃውንት ቅዳሴ ከቅዳሴ ሐአዋርያትና ከቅዳሴ እግዚእ ሌላ በሆኑት ቅዳሴያት ማለት ነው፦
“ ሥጋሁ ለአማኑኤል አምላክነ ዘበአማን ዘነሥአ እም እግዝእተ ኵልነ ማርያም ” ወይም በአማርኛ “ከሁላችን እመቤት ከማርያም
የነሣው እውነተኛ የሚሆን የአምላካችን የአማኑኤል ሥጋ ይህ ነው” ሲል፤ ተቀባዩ ወይም ቆራቢው “አሜን ይላል ወይም እያሉ
ይቀበላሉ።
ንፍቁ ወይም ሁለተኛው ካህን ክቡር ደሙን ለካህናቱ ማለትም ለዲያቆናቱ ሲያቀብል፦ “ዝንቱ ጽዋዐ ሕይወት
ዘወረደ እምሰማያት ክቡር ደሙ ለክርስቶስ” ወይም በአማርኛ “ይህ የሕይወት ጽዋ ከሰማይ የወረደ የክርስቶስ ክቡር ደሙ ነው” ሲል፣ ተቀባዮቹ ዲያቆናት
አሜን ወአሜን እያሉ ይቀበላሉ፡፡
ዲያቆኑ ክቡር ደሙን የያዘውን ጽዋ ከካህኑ እጂ ሲቀበል፦ “ጽዋዐ ሕይወት እትሜጦ ወስመ እግዚአብሔር እጼውእ” “ ወይም በአማርኛ የሕይወት ጽዋን እቀበላለሁ የእግዚአብሔርንም ስም እጠራለሁ” ይላል።
ከመቅደስ ውጭ በሚያቆርቡ
ጊዜ የካህናት አዋጅና የሚቆርቡት ፆታ ምእመናን ተሰጦ ወይም መልስ
v ካህኑ ወይም አንደኛው
ካህን ቅዱስ ሥጋውን ሲያቀብል ከማቀበሉ በፊት “ዝንቱ ውእቱ ሥጋሁ ለክርስቶስ ዘተውህበ
በእንቲአነ ወይም በአማርኛ ስለ ኃጢአታችን የተሰጠ የክርስቶስ ሥጋው ይህ
ነው” ይላል። ተቀባዩ ፆታ ምእመን መናገር የሚችል ከሆነ ራሱን ዝቅ አድርጎ አሜን ሲል ያቀብለዋል። የክርስትና አባቶችና
እናቶች ራሳቸው መልስ መስጠት ለማይችሉ የክርስትና ልጆቻቸው አሜን
ይላሉ።
v ዲያቆኑ ወይም አንደኛው ዲያቆን ክቡር ደሙን ሲያቀብል ከማቀበሉ በፊት “ዝንቱ ውእቱ ደሙ ለክርስቶስ
ዘተክእወ በእንቲአነ ወይም በአማርኛ ስለ እኛ የፈሰሰው
የክርስቶስ ደም ይህ ነው!” ይላል። ተቀባዩ ወይም ቆራቢው/ወይም ቆራቢዋ/ መናገር የሚችል ወይም የምትቺል ከሆነ ራሱን
/ራሷን ዝቅ አድርጎ/አድርጋ አሜን ሲል/ስትል ያቀብለዋል/ያቀብላታል። የክርስትና አባቶችና እናቶች ስልሕጻናቱ አሜን ይላሉ።
v
ቅዱስ ሥጋውን እና ክቡር ደሙን የሚቀበሉ ጾታ ምእመናን ሁሉ፦ሥጋውን ሲቀበሉ አንድ ጊዜ፤ ደሙን ሲቀበሉ ሁለት ጊዜ በድምሩ ሦስት ጌዜ “አሜን” ይላሉ።
ምንጭ መጽሐፈ ቅዳሴ ገጽ
125-128 እና የሥርዓት መጻሕፍት
No comments:
Post a Comment