Blog Archive

Tuesday, August 26, 2014

Filseta Lemariam

ፍልሰታ፡ ለማርያም
“ኢየሱስም በዚህ መጽሐፍ ያልተጻፈ ሌላ ብዙ ምልክት በደቀመዛሙርቱ ፊት አደረገ” ዮሐንስ 20፡30

“የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጄ ይሆን ዘንድ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ
ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል”2ኛ ጤሞቴዎስ 3፡16-17

የፍልሰታ ለማርያም ታሪክና ትርጉም ባጭሩ።
ፍልሰታ፡ለማርያም
የስም ትርጓሜ

ፍልሰት የሚለው ቃል ነው ፍልሰታ የሆነው
ፍልሰት ፈለሰ ተሰደደ ፤ ከቦታ ቦታ ተዘዋወረ ከሚለው የግእዝ ግሥ የወጣ ስም ወይም ባእድ ዘር ይባላል
ፍልሰት ማለት መሰደድ ከቦታ ቦታ መዘዋወር ወይም ዝውውር ማለት ነው
ፍልሰ-ታ የመጨረሻዋ ፊደል ወደ ወደ ራብእ ፊደል መቀየሯ የባለቤት ዝርዝርን  ወይም ባለቤትነትን ለማመልከት ነው።
ማለትም ከቦታ ቦታ የተዘዋወረውን ወይም የተሰደደውን ለመጠቆም ነው ።
 በመሆኑም ፍልሰታ የሚለው ቃል ብቻውን ሊጠቀስ አይችልም። ፍልሰታ ብለን ወደፊት የሚከተል ቃል ሁል ጊዜም መኖር አለበት።
 አንድ ፊደልና ወይም “ለ” የተባለው ሆሄ እና አንድ ስም መኖር አለበት በዚህ ርእሳችን ላይ ማርያም የሚለው ቃል።
 ስለዚህ “ፍልሰታ ለማርያም” (“ፍልሰታ ለማርያም ድንግል፤ ፍልሰታ ለማርያም ወላዲተ አምላክ) ሊባልም ይችላል።
የማርያም ከቦታ ቦታ መዘዋወር ማለት ነው፡

የእመቤታችን ቅዱስ ሥጋ መጀመሪያ ማለትም ከዚህ ዓለም በሞተ ሥጋ ከተለች ጊዜ ጀምሮ ቅዱስ ሥጋዋ ካረፈበት ወይም
 ከነበረበት ቦታ በሐዋርያት ጸሎት ምክንያት ወደ ሌላ ቦታ መሄዱን ለመናገር ነው።

የበአሉ ዋና ዋና ክፍሎች፡

ቅድስና የባሕርዩ የሆነ ልዑል እግዚአብሔር

ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ፤
ቅዱሳን ሐዋርያት እና እውነተኛ  ጸሎት፡ የሚሉት ናቸው።

ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም  የታሪኩ ዋነኛ ምክንያት ናት
ልዑል እግዚአብሔር  የታሪኩ መፍትሄ ነው
ቅዱሳን ሐዋርያት በጸሎት መሣሪያነት ታሪኩን የሠሩ ናቸው
ጽሎት ፡መሣሪያ መሣሪያ ነው።

መልእክት፡
እግዚአብሔር ትእዛዙን ጠብቀው ፈቃዱን አሟልተው በትክክል ከጠየቁት የጠየቁትን የሚሰጥ  ለጋስና ቸር አምላክ ነው
ጸሎት  በፍጡራን እና በፈጣሪ መካከል የመግባቢያ ቋንቋ ነው ወይም መሣሪያ ነው። በጸሎት የማይገኝ ነገር የለም።
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም “ለምኑ ይሰጣችኋል፤ መዝጊያውን አንኳኵ ይከፈትላችኋል” በማለት ለተከታዮቹ በፍፁም እምነት፤
ትክክለኛውን ልመና ከለመኑ መልስ እንደሚሰጣቸው ቃል ገብቷል።በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙ ሰዎች ወይም
ቅዱሳን በጸሎት አማካኝነት የሚፈልጉትን አግኝተዋል፤ ከኃጢአት ነጽተዋል፤ ከሕመማቸው ተፈውሰዋል፤
 ከሙታን ተነሥተዋል። በአጠቃላይ በጸሎት መሣሪያነት ታላላቅ ድንቅና ተአምራት ተሠርተዋል።
በእምነትና በንጹህ ልብ የሚጸለይ ጸሎት ተራራ እንኳን ማንቀሳቀስ እንደሚችል መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል።

ሐዋርያት የፆሙት ሁለት ሱባኤን ነው ሁለት ሱባኤ የሚባለውም 7፤7 አሥራ አራት ቀናት ነው። (በዚህ ጾም ላይ) ስለዚህ

ነሐሴ አንድ ቀን ጀመሩ
ነሐሴ 14 ጨረሱ ወዲያውኑ ጥያቂያቸው ተመልሶላቸው የሚፈልጉትን የእመቤታችንን ቅዱስ ሥጋ አገኙ፡
ወዲያውኑ በጌቴሴማኒ ቀበሯት
በሦስተኛው ቀን ነሐሴ 16 እንደ ልጇ እና እንደ አምላኳ ተነሥታ አረገች፡
ስለዚህ፡
ፍልሰታ ለማርያም/የማርያም ከቦታ ወደ ቦታ መዘዋወር          

ትንሣኤሃ ለማርያም/የማርያም ትንሣኤ

እርገታ ለማርያም/የማርያም እርገት
የሚባሉትን ሦስት የመታሰቢያ በአላት እናስባለን ማለት ነው።

በመሆኑም የጸሎትን ታላቅ ሃይልና የእግዚአብሔርን ጸሎት ሰሚነት የምንገነዘብበት ጌዜ ነው።

እመቤታችን በ5486 ቅድመ ክርስቶስ ተወለደች

በ64 ዓመቷ ጥር 21 ቀን 50ዓ/ም አረፈች እስከ ነሐሴ 14 50 ዓ/ም ድረስ ቅዱስ ሥጋዋ ከሐዋርያት ተሠውሮ በመልአኩ
አማካኝነት ወደ ብሔረ ሕያዋን ተወስዶ እስከ ነሐሴ 14 ቀን በዚያ ከቆየ በኋላ በቅዱሳን ሐዋርያት ጸሎት
በቅዱስ እግዚአብሔር ፈቃድ ነሐሴ 14 ቀን 50ዓ/ም ለሐዋርያት ተሰጠ፤ቅዱሳን ሐዋርያት ወዲያውኑ በ14
በጌቴሴማኔ በመቃብር አሳረፏት፤ በ3ኛው ቀን ነሐሴ 16 ተነሥታ ወዚያው ቀን አረገች።

የታሪክና የሊቃውንት መጻሕፍትን ይመልከቱ።



No comments:

Post a Comment