የግእዝ ትምህርት ክፍል 21
መራኁት
መራኁት ማለት?
¨ መራኁት ማለት መክፈቻዎት ማለት ሲሆን “መርኆ” የሚለው ቃል ብዜት ወይም ብዙ ቁጥር ነው
¨ መርኆ
¨ = መክፈቻ ማለት ነው
¨ መራኁት =
መክፈቻዎች ማለት ነው ለብዙ ቁጥ
መራኁት የሚባሉት ሆሄያት ሲሆኑ 5 ናቸው
¨ ግእዝ፤ (መጀመሪያ ወይም 1ኛ)
¨ ራብዕ፤ (አራተኛ ወይም 4ኛ)
¨ ሐምስ፤ (አምስተኛ ወይም 5ኛ)
¨ ሳድስ፤ (ስድስተኛ ወይም 6ኛ)
¨ ሳብዕ፤ (ሰባተኛ ወይም 7ኛ)
ናቸው።
ዘርግስ በ5ቱ መራኁት ብቻ ይጀምራል
መራኁት በአምስቱ ሆሄያት ሲጀምሩ
የሚያሳይ ምሳሌን በሚቀጥሉት 5
(አምስት) ገጾች ይመልከቱ
ዘር ግሥ በካዕብና በሳልስ አይነሣም
መራኁት በግእዝ ሆሄ ሲጀምሩ
¨ ሐለመ
¨ ከፈለ
¨ አእመረ
¨ ተንበለ
መራኁት በራብዕ ሆሄ ሲጀምሩ
¨ ባረከ
¨ ሣረረ
¨ ፃዕደወ
መራኁት በሐምስ ሲጀምሩ
¨ ሤመ
¨ ኄለ
¨ ዔለ
መራኁት በሳብዕ ሲጀምሩ
¨ ቆመ
¨ ሖረ
¨ ጾመ
¨ ሆከ
መራሁት የማይጀምሩባቸው ወይም የማይነሡ ባቸው ሆሄያት
¨ ካዕብ (ሁለተኛ ሆሄ)
¨ ሳልስ (ሦስተኛ ሆሄ)
በነዚህ ሆሄያት ዘር ግሥ አይጀምርም
የቃላት ትርጉም
¨ ሐለመ=
¨ አለመ (ሕልም)
¨ ከፈለ=
¨ ከፈለ (መክፈል) አደለም ይሆናል (ዕድል)
¨ አእመረ=
¨ አወቀ
¨ ተንበለ=
¨ ለመነ፤ አማለደ
¨ ባረከ=
¨ ባረከ፤ መረቀ
¨ ሣረረ=
¨ መሠረተ፤ ተከለ፤ ሠራ
¨ ፃዕደወ =
¨ ነጣ(ነጭ)
¨ ሤመ=
¨ ሾመ
¨ ኄለ=
¨ ወጣ፤ እልል አለ፤ ደነፋ
¨ ዔለ=
¨ ዞረ
¨ ቆመ=
¨ ቆመ
¨ ሖረ=
¨ ሄደ
¨ ጾመ=
¨ ጾመ
¨ ሆከ=
¨ አወከ
No comments:
Post a Comment